Friday, January 26, 2007

ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ሁለት ሺ አዲሰ አመት ለመሄድ ተዘጋጅተዋል እን?

ለመሆኑ ለኢትዮጵያ ሁለት ሺ አዲሰ አመት ለመሄድ ተዘጋጅተዋል እን?

እኛ ባዎጣነው የቀን መቁጠሪያ መሰረት ለአዲሱ አመት የሚቀሩት ቀናት 257 ቀናት ብቻ ናቸው፡፡ ታዲያ እርስዎስ ለዚህ ቅዱስ ቀን ከዘመድ ወዳጅ ጋር አብረው ለማሳለፍ ጉዝወን እያስተካከሉ ነው እን? ያው ጉዞ ሲባል ትንሽ ሰለሌለው ትንሽ ገንዘብ ከመቋጠር ጀምሮ፣ ለዘመድ አዝማድ የሚሆን ስጦታ መግዛት፣ ስራ ማስፈቀድ፣ ትቶ የሚሄዱትን ቤተሰብ ደግሞ ቦታ፣ ቦታ ማስያዝ፣ የመብራት፣ የጋዝ፣ የቴሌፎን፣ የመኪና ኢንሹራንስ፣ የክሬዲት ካርድ ክፍያ፣ ሌላም ሌላውም በወቅቱ መከፈሉን፣ ደብዳቤዎ ተቀባይ ማግኘቱን ሁሉ ማስተካከሉ ትልቅ የራስ ምታት ነው፡፡
ይህን ሁሉ ጣጣ ከጨረሱ በኋላ ደግሞ ትልቁ ጥያቄ መቼ ነው ትኬት መግዛት ያለብኝ የሚለው ሲሆን ከዚያ ደግሞ የፓሰፖረት እና የቪዛ ማውጣቱ ጉዳይ ነው ናላዎን የሚያዞረው፡፡ እስኪ ነገሮችን እንድ ባንድ እንመልከት፡፡

ያው የስራችን ጸባይ ሆኖ በየቀኑ ከሀገራችን ወንድምና እህቶች ጋር ስለምንገናኝ ለአዲሱ አመት እሄዳለሁ ያለን ሰው ሁሉ ከሄደ አሜሪካ ባዶዋን መቅረቷ ነው፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ ነው ያለው፡፡ የሚገርመው ግን እንከ አሁን ልቡ ቆርጦ ትኬቱን የገዛው ሰው በጣም ትንሽ ነው፡፡ ለምን ብትሉ ተጓዡ የሚጠብቀው መቼ ነው ትኬት የሚረክሰው የሚለውን መልስ ለማግኘት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከባድ ጥያቄ ሲሆን መልሱ ደግሞ ይረክሳል ብላችሁ ስትጠብቁ ቦታ እንዳታጡ ነው፡፡

በአብዛኛው ተጓዥ ለአዲሱ አመት አዲስ አበባ ለመድረስ የሚፈልገው ከአዲሱ አመት ከሳምንት በፊት ነው፡፡ ይህም ማለት ደግሞ ከ ሴፕቴምበር 1 – 5 ባለው ጊዜ ውስጥ ማለት ነው፡፡ እርስዎም እቅድዎ በነዚህ ቀናት ውስጥ ለመድረስ ከሆነ ከወዲሁ መዘጋጀት ያለብዎት ይመስለናል፡፡ ሌላው ደግሞ መስከረም የጋብቻ ወር ስለሆነ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንደሚሉት ለሰርግ የሚሄደው ተጓዥ ቁጥር በጣም ብዙ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ሰርገኛውም እንደ ሌላው ትኬቱን እስከአሁን አልገዛም፡፡

ስራችን ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ እንዳይሆን ከወዲሁ ትርምስ ውስጥ ከመግባት ጉዝዎን ማስተካከሉ እፎይ ብለው እንዲቀመጡ ደርገወታል፡፡ ሌላው ተጓዡ በብዛት ያልተረዳው ደግሞ ይህን አዲስ አመት ለማክበር የምንሄደው እኛ (ኢትዮጵያዊያን) ብቻ ሳንሆን ሌሎችም የኢትዮጵያ ዘመድ ወዳጆች መሆናቸውን ነው፡፡ እነዚህ የኢትዮጵያ አፍቃሪዎች ጉዟቸውን በቡድን፣ በቡድን ሆነው ቀደም ብለው ስለሚያዘጋጁ ከወዲሁ ትኬታቸውን፣ ሆቴላቸውን ሁሉንም ነገር ቆርጠው ነው ቁጭ ያሉት፡፡ታዲያ እርስዎስ ምን እያደረጉ ነው?

ከሙያና ከልምድ አንፃር እኛ ለእርስዎ የምንመክረዎ ነገር ቢኖር ቅድመ እግጁቱን ከወዲሁ ያጠናቁ ነው፡፡ ከዚህ በታች ያሉትን ነገሮች ከወዲሁ ማስተካከለሉ ጉዝዎን እራስ ምታት የሌለበት ጤናማ ጉዞ ያደርገዋል፡፡

የሚሄዱበትን ቀን ከወዲሁ ይወስኑ፡፡ ከመወሰንዎ በፊት ግን እነዚህን ከዚህ በታች ያሉትን ነገሮች ያስተካክሉ፡፡
ከስራዎ በቂ ፍቃድ ማግኘትዎን በቅድሚያ ያረጋግጡ (ይህ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡)
እርስዎ ወይም ልጅዎ ከትምህርት ቤት አቋርጠው የሚሄዱ ከሆነ ትምህርት ቤት መቼ እንደሚዘጋና መቼ እንደሚከፈት ይጠይቁ፡፡
እርስዎ በሄዱ ጊዜ ቤትዎን፣ ድብዳቤዎን፣ ሌሎችንም ክፍያዎች እንደርስዎ ሆኖ የሚጠብቅልዎ ሰው ያዘጋጁ፡፡ (ዞሮ ዞሮ መግቢያዎ ቤትዎ ነወና)
መቼ መመለስ እንዳለብዎ ከወዲሁ ይወስኑ፡፡ አይወላውሉ፡፡ ቪዛዎ፣ ግሪን ካርድዎን፣ ሌላውም ነገር እናዳይቃጠል አደራ፡፡ እንደወጡ እንዳይቀሩ፡፡ ለመግባት ፍተሻው ጥብቅ ነው፡፡
ፓስፖርት ከሌልዎ ፓስፖርትዎን ያውጡ፡፡ የአሜሪካ ፓስፖርት እሰከ አምስት ሳምንታት ሊወስድ ይችላል፡፡ ህፃናትም ሆነ አዋቂው ፓስፖርት ያስፈልጋቸውል፡፡
በትራቭለርስ ዶክመንት (Traveler’s Document) የሚሄዱ ከሆነ ከስድስት ወር በፊት ያመልክቱ፡፡ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ለምን ክል ጊዜ መቆዬት እንደሚችሉ ያረጋግጡ፡፡
የኢትዮጵያ አዲስ ፓስፖርት ከፈለጉ ከወዲሁ ያመልክቱ (እስከ ሶስት ወር ሊወስድ ይችላል)
የኢምግሬሽን ወይም የፍርድ ቤት ቀጠሮ ካለዎት ቀኑን በትክክል ይወቁ፡፡
ከሀኪም ጋር ቀጠሮ ካለዎት ከወዲሁ ይወቁ፡፡
ለጉዝዎ ምን ምን አይነት ክትባት እንደሚያስፈልግዎት ከወዲሁ ይዎቁ፡፡
በተለይ ከሕፃናት ጋር የሚሄዱ ከሆነ ክትባታቸውን መጨረሳቸውንና እርሰዎ ወደ አፍሪካ እንደሚሄዱ ለዶክተርዎ ያስታውቁ፡፡ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደ አፍሪካ/ኢትዮጵያ ተጓዦች የተለየ ክትባት ሊኖር ይችላል፡፡
ሌሎችንም አስፈላጊ ነገሮችን ያጠናቁ፡፡
መጨረሻ ትኬትዎን ይግዙ፡፡

ስለ ትኬት መግዛት፡፡
ወደ ኢትዮጵያ የሚሂዱ አየር መንገዶች የተወሰኑ ናቸው፡፡ እነርሱም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሉፍታንዛ፣ ኬኤልኤም፣ ኤሜሪትስ፣ ብሪቲሸ ሲሆኑ እያንዳንዳቸውም ደካማም ሆነ ጠንካራ ጎን አላቸው፡፡ ወሳኙ እርስዎ ነዎት፡፡
ፍላጎትዎ ገንዘብ ለመቆጠብ ከሆነ እረከስ የሚላው ኢምሬትስ ሲሆነ ነገር ግን ዱባይ ላይ ከ አንድ ቀን በላይ ይቆያሉ፣ ብሪቲሽ ደግሞ አንዳንዴ ለንደን ላይ ማደር ሲኖር እንደ እርስዎ የመኖሪያ ፍቃድ ሁኔታ ታይቶ ቪዛ ሊያስፈልግዎት ይችላል፣ ለሁሉም ለብሪትሽ ኢንባሲ ደውለው ያረጋግጡ፡፡ ጊዜ ወርቅ ነው ሰለሚባል በጉዝዎ ላይ እንግልት እንዳይደርስብዎት ከወዲሁ ያስቡበት
፡፡ በተለይ ደግሞ ከልጆች ጋር የሚጓዙ ከሆነ ለትንሽ ገንዘብ ብለው ያልሆነ ጉዞ እንዳይመርጡ፡፡

ለምሳሌ የእኛ ደንበኞች ከ 99 ፐርሰንት በላይ የሚጓዙት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሲሆን የተለያዮ ቅሬታዎች ቢኖሩም ነገሮች ቀስ በቀስ እየተስካከሉ ነው፡፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥሩነት፣ አንድ ከተማ ላይ የመቆዩት በጣም ትንሽ ነው፡፡ ለምሳሌ ከሳንድያጎ የሚነሳ ሰው ሻንጣውን አንዴ ሳንድያጎ ካስገቡ በኋላ ሰለሻጣዎ የሚያስጨንቀውት ነገር የለም፣ ሻንጣው ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ እርስዎ ቀጥታ ወደ ዋሽንግተን ሄዶው ከአራት ወይም ከአምስት ሰዓታት ቆይታ በኋላ ወደ ሀገር ቤት በቀጥታ መጓዝ ሲሆን ለብዙ ደንበኞቻችን አመቺ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ አንዳንዴ ጥቃቅን ቅሬታዎችን ብንሰማም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የዚህን የአዲስ አመት ጉዞ በሚያስደስት ሁኔታ እንደሚያካሂደው ባለሙሉ ተስፋ ነን፡፡ ሉፍታናዛ በብዙዎች ዘንድ የተደነቀ ቢሆንም በጣም ውድ ነው፡፡ ሌላው ቨርጂን አትላንቲክ ሲሆን ችግሩ ከብዙ ከተማዎች አገልግሎት አይሰጥም፡፡

ሌላው መጠንቀቅ ያለባቸሁ ነገር ስንት ሻንጣ እና ምን ያክል ክብደት መያዝ እናዳለባችሁ ማወቁ ነው፡፡ ለምሳሌ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚፈቅደው ሁለት ሻንጣ እያንዳንዱ 50 ፓውንድ ነው፡፡ ነገር ግን በበለጠ ለመረዳት እባክዎ ከመነሳትዎ በፊት የሚሄዱበትን አየር መንገድ ደውለው ይጠቁ ፡፡

በአሁኑ ወቅት ባለው የጉዞ ጥብቅነት የተነሳ እባክዎ ትኬትዎን ከመቁረጥዎ በፊት ስምዎ ልክ ፓስፖርትዎ ላይ እንዳለው መፃፉን ያረጋግጡ፡፡ ሌላው ትኬትዎን በጥንቃቄ ያስቀምጡ፣ ይህም ማለት ለምስሌ ትኬትዎ በአጋጣሚ ቢጠፋ ለመተካት በጣም አስቸጋሪ ስለሆነ በደህና ቦታ ያስቀምጡት፡፡ በዚህ የአዲስ አመት ጉዞ አዬር መንዶችም ሆነ የጉዞ ወኪሎች በጣም ስራ ስለሚበዛባቸው የእርስዎ ትብብር አስፈላጊ ከመሆኑም ባሻገር በተቻለዎ መጠን ቅድመ ሁኔታዎችን ከወዲሁ ያሟሉ፡፡ ለምሳሌ
· ትኬትዎ ባለው ቀንና ሰአት ለመሄድም ሆነ ለመምጣት ይሞክሩ፡፡
· ባለቀ ሰዓት ሀሳብዎትን አይለውጡ፡፡
· አላስፈላጊ ባልሆነ ነገር በትንሹም በትልቁም አይጨቃጨቁ፡፡
· ትግስት ይኑርዎት፡፡
· ህጉን ይከተሉ፡፡
· የሚገዙት ትኬት ያለውን ሪሰተሪክሽን “restriction” ጠንቅቀው ይወቁ፣ ከመግዛትዎ በፊት የጉዞ ወኪልዎን ያማክሩ፡፡
· ከበረራዎ 72 ሰዓታት በፊት ስለ በረራዎ አየር መንገዱን ጠይቀው በረራዎን ኮንፊርም “confirm ” ያድርጉ፡፡
· አዲስ አበባ ከደረሱ በኋላ ለመመለስ ሀሳብዎን በሆነ ባልሆነው አይለውጡ፡፡ በጣም ብዙ ተሳፋሪ ሰለሚኖር መጉላላት እንደሚኖር ከወዲሁ ይገምቱ፡፡ ስለዚህ ባሉት ቀንና ሰዓት ጉዝዎትን ያድርጉ፡፡
· ጓዝ አያብዙ፣ ከመንገደኞቻችን እንደምንሰማው ሁሉም ነገር አገር ቤት ሰላለ ገንዘብዎን በሆነ ባልሆነው ከዚህ አይጨርሱ፡፡ ህዝቡ የሚፈልገው ገንዘብ ሰለሆነ ገናዘቡን ቢሰጡት በጣም ይጠቅማል፡፡
· ሲመለሱም በተቻለዎ መጠን ጓዝ አያብዙ፣ ምክንያቱም እርስዎ ብቻዎን ሰለሚመጡ ሻንጣዎትን በራስዎ ወደ ጉምሪክ መግፋት አለብዎት፡፡
· ይህን አመጣለሁ፣ ይህን እወድዳሁ እያሉ ለሰው ቃል አይግቡ፡፡ እራስዎትን ሊያመዎት ስለሚችል፡ ጉዝዎ ለራስዎ ብቻ ያተኩሩ፡፡

ሌላው ከአንድ የጉዞ ወኪል ወደ አንዱ በመደወል ጊዜዎትን አይግደሉ፡፡ በአብዛኛው ሊያተርፉ የሚችሉት ከ 30.00 ዶላር በላይ ሰለማይበልጥ እራስዎን ከአንድ ቦታ በላይ በማስመዝገብ ሌላው እድል እንዳያገኝ አያድርጉ፡፡ ይህ በጣም ተለመደ አስነዋሪ ተግባር ሰለሆነ፣ ትኬት በቆረጡ ጊዜ ከሌላ ቦታ የያዙትን ቦታ ደውለው እንዲሰረዝ ያድርጉ፡፡ ይህ እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል እንደተባለው ነው፡፡ ታዲያ በዚህ የአዲስ አመት ጉዞ ሁላችንም መተባበር ያለብን የውዴታ ግዴታ ስለሆን ከወዲሁ መዘጋጀቱ የማይረሳ ትዝታ ያለው ቆንጆ አመት በአል እንድናከብር ያደርገናል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ይህንን አዲስ አመት በሰላም ለማክበር ሁላችንም ቆርጠን በመነሳት፣ በዘር፣ መሃይማኖት፣ በፖለቲካ እና በሉለችም ሁኔታዎች ያለውን ልዮነት ወደ ኋላ በመተው ፍቅር፣ ወንድማማችነት፣ እህትማማችነት፣ ሰላም የሰፈነበት ታላቅ በአል ለማክበር ሀገራችንን የምናስታውቅበት አመት በአል እንዲሆን ልባችንን ንጹኅ አድርገን እንነሳ፡፡
እንቁጣጣሽ፡፡
የቦ የጉዞ ወኪል

ለሁሉም ከዚህ በታች ለእርስዎ የሚጠቅሙ ስልክ ቁትሮችን ይመልከቱ

Address
Phone
Web site
Yebbo Travel Consultant
Yebbo Travel
4535 30th St #106
San Diego, CA 92116
Tel: 619 255 5530
Fax:619 287 0409
www.yebbo.com
info@yebbo.com
Ethiopian Consulate General
3460 Wilshire Boulevard Suite 308Los Angeles, California 90010
Tel: 213 365 6651
Fax: 213 365 6670
http://www.ethioconsulate-la.org
United States Embassy in Ethiopia
P.O. Box 1014
Addis Ababa , Ethiopia
Tel. 251-1-174000
Fax 251-1-551328
Visa Section Tel. 550660
http://usembassy.state.gov/ethiopia
Embassy of Ethiopia USA
3506 International Dr. NWWashington, DC 20008
Tel: 202 364-1200Fax: 202 686-9551
http://www.ethiopianembassy.org/
Embassy of Ethiopia Canada
#210-151 Slater StreetOttawa, Ontario, CANADA K1P 5H3
Tel:613.235.6637 Fax:613.235.4638
http://www.ethiopia.ottawa.on.ca/
British Airways

1-800-403-0882
http://www.ba.com
UNITED

1-800-538-2929
http://www.united.com/
Continental

1-800-523-3273
http://www.continental.com /
Lufthansa

Tel: 00251-1-51666 (AA)
Fax 00251-1-512988 (AA)
http://www.lufthansa.com/
Ethiopian Airlines (US)
336 east 45th street, 3rd fl,
New York, NY10017
Tel: 212-867-0095
1 800-445 2733 Fax : 212-692-9589
http://www.flyethiopian.com /
The British Consulate General
11766 Wilshire Blvd, Suite 1200Los Angeles CA 90025-6538
Tel: 310 481-2900Fax: 310 481-2961
http://www.britainusa.com

No comments: